የሃይማኖት ተቋማት ስም ወይም የአርማ ለውጥ/ማሻሻል

የአገልግሎት ገለጻ
 • የሃይማኖት ተቋሞች እየተጠሩበት ያለውን የመጠሪያ ስም ወይም እየተጠቀሙበት የነበረውን አርማ መለወጥ ወይም ማሻሻል ሲፈልጉና ጥያቄው በሃይማኖት ተቋሙ የበላይ አካል በቃለ ጉባዔ ውሳኔ ውሳኔ አግኝቶ ሲቀርብ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
መሟላት የሚገባቸው ዶክመንቶች
 • የአገልግሎት ጥያቄ ማመልከቻ
 • የስም ወይም አርማ ለውጥ /ማሻሻያ ያስፈለገበት ምክንያት በሃይማኖት ተቋሙ የበላይ አካል የፀደቀበት ቃለ ጉባኤ
 • የሚለወጠው/የሚሻሻው ስም ወይም ዓርማ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ተዘጋጅቶ የቀረበበት ሰነድ
 • የዓርማው ቅርጽና ይዘት በሶፍት ኮፒ በሲዲ
 • ጉዳዩን እንዲያስፈጽሙ በሃይማኖት ተቋሙ የተወከሉት ተወካይ የውክልና ማስረጃ
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች
 • ከላይ በተራ ቁጥር ሦስት የተመለከቱት ሁኔታዎች መሟላታቸውና ህጋዊ መሆናቸው ይመረመራል
 • የተጓደሉና የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ እንዲስተካከሉና እንዲሟሉ ይደረጋል፡፡
 • መስተካከልና መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች /ነገሮች መሟላታቸው ሲረጋገጥ የድጋፍ ደብዳቤው ይዘጋጃል
 • በወጣው ጋዜጣ መሰረት ተቃዋሚ ካለ ጉዳዩ በህግ አግባብ እንዲታዩ ይደረጋል፤ተቃዋሚ ከሌለ ስም ወይም ግርማ ለውጡ ማሻሻው እንደአግባብነቱ የምክር ወረቀት ወይም ደብዳቤ ይዘጋጃል
 • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፈሉ ይደረጋል
 • የተዘጋጀው የምስክር ወረቀት ወይም ደብዳቤ በመ/ቤት በኩል ወጪ ሆኖ ለህጋዊ ወኪል ይሰጣል፡፡