የመንግስታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር

የአገልግሎት ገለጻ
  • ለውስጥና ለውጭ ባለጉዳዮች በኢትዮጵያ ህብረብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች መስጠት፤
  • በኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት አወቃቀርና ህገ-መንግስታዊ መሰረቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት፤
  • የስልጠና ፍላጎት ለሚያሳዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች(ዕጩ ተመራቂዎች)በህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ጋርተያዥነት ያላቸውን የጥናትና ምርምር አርዕስቶችን መለየትና መጠቆም
  • ከውስጥና ከውጭተገልጋዮች(ባለድርሻ አካላት) ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፤
  • ሕገ-መንግስታዊ የፌዴራል ስርዓቱን ለማጠናከር፤ሀገራዊ ልማትንና ሰላምን ለማረጋገጥ እና የዲሞክራሲያዊ ግንባታ ስራዎችን ለማጎልበት የሚያግዙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፎችን ማዘጋጀትና ለባለድርሻ አካላት መሰራጨት፤
  • ሕገ-መንግስታዊ የፌዴራል ስርዓቱ ማዕቀፍየመንግስታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችየሚጠናናከሩበትን አማራጮች የሚያስችሉ ጥናቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች
  • ከባለድርሻ አካላት አገልግሎቶችና መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን፤በመድረኮች እና በመጽሄትና በብሮሸር፤
  • ከባለድርሻ አካላት የአገልግሎት ፍላጎትና ቅሬታ መቀበልና ግብረ-መልስ መስጠት፤