የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት

የአገልግሎት ገለጻ

በሃይማኖት ተቋማት ተመዝግበውና ወቅታዊ ዕድሳት አድርገው የሚሰሩ የሃይማኖት ተቋማት ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት ለሚሰሩአቸው ተግባራት ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለማግኘት የተለያዩ አግባብነት ላላቸው አካላት የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ሲጠይቁ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት ፡-

 • ለሃገር ውስጥ የተለያዩ ባንኮች፣በሃይማኖት ተቋሙ ስም የባንክ ሂሳብ ለመክፈት፣
 • ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ለውጭ ሃገር ሰዎች ለሃይማኖታዊ ተግባር የሥራ ፈቃድ ለማውጣት፣
 • ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት፣ በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት የተመረጡትን የሃይማኖት የተቋሙን የሥራ መሪዎች/ኃላፊዎች ለማሳወቅ፣
 • ለተለያዩ የማተሚያ ድርጅቶች የገቢና ወጪ ደረሰኞችን፣ ማኅተሞችንና ቲተሮችን ለማሳተም፣
 • ለፕሬስ ድርጅት፣ በምዝገባ ወይም በስም ለውጥ ጊዜ የሃይማኖት ተቋሙን ስም፣ ሎጎ/ምልክት ለማስመዝገብ እንዲሁም በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ መሠረት የሃይማኖት ተቋሙ ህልውና ያበቃ መሆኑን ለማሳወቅ፣
 • ለፌደራልና ለክልል የፍትህ፣ የአስተዳደር/ የአስፈጻሚ አካላት፣ የሃይማኖት ተቋሙ መመዝገቡን ህጋዊ መሆኑንና መሰል ጉዳዮችን እንዲያቁት ለማድረግ፣
መሟላት የሚገባቸው ዶክመንቶች
 • የአገልግሎት ጥያቄ ማመልከቻ
 • የጉዳዩን ዓይነት፣እነማን እንደተወከሉ ለየትኛው አካል እንደሚፃፍና ሌሎች ዘስፈላጊ መረጃዎችን የያዘ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በሚመለከተው የሃይማኖት ተቋሙ አካል የፀደቀ ቃለ ጉባኤ
 • ጉዳዩን ለማስፈጸም የተወከሉት ግለሰብ የውክልና ማስረጃ
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች
 • ከላይ የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውና ህጋዊነታቸው ይመረመራል
 • የተጓደሉና የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ እንዲስተካከሉና እንዲሟሉ ይደረጋል፡፡
 • መስተካከልና መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች /ነገሮች መሟላታቸው ሲረጋገጥ የድጋፍ ደብዳቤው ይዘጋጃል
 • የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል
 • የተዘጋጀው የድጋፍ ደብዳቤ በመ/ቤት በኩል ወጪ ሆኖ ለህጋዊ ተወካዩ ይሰጣል፡፡