Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

በሰላም አብሮ የመኖር እሴታችን ቀጣይነቱ መረጋገጥ አለበት

የሃይማኖት ተቋማት የሰላም ሞዴል እንዲሆኑ የውስጥ ሰላማቸው መረጋገጥ አለበት

የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የአማራ ክልል የመንግስት መዋቅር አመራርና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር ከታህሳስ 11 እስከ 13 በባህርዳር ከተማ ውይይት አድርገዋል፡፡

የአማራ ክልላዊ መንግስት አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንዳሉት የህዝቦች አብሮ የመኖር እሴት እንዲጎለብትና በህገ መንግስቱ የተረጋገጠው የሃይማኖት ነጻነትን የሚጻረር የአክራሪነት አመለካከትና ተግባር እንዲወገድ መንግስትና ህዝብ ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው በቀጣም ተከታታይ የሆነ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም የሃይማኖት መሪዎችም ሆኑ የመንግስት አካሉም ከመድረኩ ግንዛቤ በመጨበጥ በጸረ አክራሪነት ትግሉ ላይ ተሳታፊ በመሆን አመለካከቱን በተግባር በመታገል የአገሪቱን ህዳሴ ጉዞ እንቅፋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ማድረስ እንዲችሉ ለተሳታፊዎች ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሃጂ መስኡድ አደም በበኩላቸው በአገራችን ለዘመናት የኖረው የሃይማኖቶች መቻቻል በሰላም አብሮ  የመኖር አኩሪ አሴትን በማዝለቅ የሀገርን ህልውና ፈተና ላይ የሚጥለውን የአክራሪነት አደጋ ለመታገል ከሃይማኖት መሪዎች በላይ የሚሆን አለመኖሩን በመግለጽ የተሳሳቱ መልእክቶችን በትክክለኛ በመተካት፣ ቅንጀትዊ አሰራርን ተግባራዊ በማድረግና የአክራሪውን ተለዋዋጭ ባህሪ  በንቃት በመከታተል የሚመክቱ ስልቶችን በመጠቀም  የአገራችንን  ሰላም ለመጠበቅ መንፈሳዊ  ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጉባኤው ያስገነዝባል ያሉ ሲሆን በሀይማኖት ተቋማት የሚነሱ ጥያቄዎች በወቅቱ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የብዙሃንና ሙያ ማህበራትና የሃይማኖትና  ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ አቶ አወል ወግሪስ የዘላቂ ሰላምና ልማት ተጠቃሚ መሆን የሚቻለው በመደጋገፍ የተመሰረተ ግንኙነት ሲኖሩ ነው፡፤ ካሉ በኋላ ብልሹ አሰራር፤ ከአክራሪነትና ጽንፈኝነት የሚመነጩ፣ ድህነትና ኋላ ቀርነት የሚባብሷቸው ችግሮቻችን በመገንዘብ መንግስትና የሃይማኖት መሪዎች ከህዝቡ ጋር በመተባበር ሰላምና ልማትን የጋራ አጀንዳ አድረገው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡ ሴቶችና ወጣቶች ለሰላምና ልማት ያላቸውን አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ የጸረ ሰላም ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በዚህም ሂደት አለመግባባቶችን በውይይት ብቻ መፍታት አስፈላጊ መሆኑና  የሃይማኖት ነክ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች አፋጣኝ መፍትሄ መስጠትም እንዳለበትም  መልእክት አስተላለፈዋል፡፡

አብሮነትና ሰላም፣ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ የሴኩላሪዝም መርሆዎችና የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት፣ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ አክራሪነትና ፅንፈኝነት አደጋና የመታገያ ስልቶች፣ ማኅበረሰብ ተኮር የፀረ-አክራሪነት ትግል ንቅናቄና የማስፈጸሚያ  ስልት፣ የማህበረሰብ ተኮር  የጸረ አክራሪነት ትግል የማስፈጸሚ ስልት እቅድ፣ የሀይማኖት ተቋማት የጤናማ ግንኙነት ጉዳዮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ለመመዝገብና ተዛማጅ አገልግሎቶች ለመስጠት የወጣ ረቂቅ መመሪያ በሳስቱ ቀናት የውይይት  መድረክ ለገለጻ የቀረቡ ጽሁፎች ሲሆኑ  የቡድን ውይይት ተደርጎቸዋል፡፡

ክትትልና ድጋፍ ሰውራው ጥብቅ ያለ አይደለም፣ትምህርትና ስልጠናው መሬት ላይ ማረፉ በጥናት እየተረጋገጠ አይደለም፣ ስልጠናዎች እስከታች ህዝቡ ድረስ ወርደው እየተሰጡ አይደለም፣ሰላም ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሁኖ ሳለ ሴሚናር ለማድረግ የበጀት ችግር አለብን፣ የመቃብር ቦታ ለማግኘት ሰው መሆን በቂ ነው፣ ወጥነት ያለው ስራ ለመስራት ራሱን የቻለ መ/ቤት ሆኖ ቢዋቀር፣ ወቅትና ችግሮች ላይ ያተኮረ ሳይሆን መሰረት ያለው ስራ ቢሰራ ውጤታማ መሆን ይቻላል፣ በቤተ እምነት ያሉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በወቅቱ እየተመለሱ አይደለም፣የተፈጠሩ አደረጃጃቶች ወይም የሃይማኖት ፎረሞች አልተጠናከሩም፣ የመስሪያ ቢሮ ችግርም አለባቸው፣ ውይይት በአመት አንዴ ሳይሆን ቢያንስ ሁለቴ መሆን ቢችል፣ የህገመንግስቱ ድንጋጌዎች እየተተገበሩ መሆናቸው መፈተሸ አለበት፣ በአንዳንድ ቦታዎች የሴኩላሪዝም መርህ እየተጣሰ ነው፣ምርጥ የመቻቻል እሴቶቻችን እየተሸረሸሩ ነው፣በአንዳንድ አካባቢዎች ሃይማቶች በእኩል አያይዋቸውም፣ ህገወጥ ተቋማት ሲገነቡ ፈጥኖ ያለመከታተል ችግር አለ፣ አንዳንድ አመራሮች ወደ እምነታቸውየመወገን ሁኔታ ይታያል የሚሉ አስተያየቶችና የሀይማኖት ነጻነት መጨረሻው ምንድን ነው፣ የሃይማት ተቋማት  እየበዙ ከሄዱ እንዴት ነው ማስተዳደር የሚቻለው፣ የሚሉ ጥያቄዎችም ከተሳታፊዎች ተነስተው የማብራሪያ ተሰጠቷል፡፡

ወደ ራስ ማድላት አለ የተባለው ተጨባጭ ችግር ነው፡፡ ለዚህም እንደ ክልል ራስ ለማየት ትግል እየተደረገ መሆኑና የመታገል ጉዳይ ወቅቱ የሚጠይቀው አጀንዳ እንደሆነ መልስ ተሰጥቷል፡፡

የግንዛቤ ማሳደጊ መድረኮች ማድረግን በተመለከተ ትክክል ነው በቀጠይ መድረኮቹ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ተብሏል፤የቅንጀት ስራውም መሻሻል እንዳለበት ተገልጽዋል፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የሃይማኖት መሪዎችም የመንግስት መዋቅሩም መስራት አለባቸው ተብሏል፡፡ በሃይማት ምክንያት አድሎ መፈጸም ተገቢ አለመሆኑም ተገልቷል፡፡ የሰላም ስራ የዘመቻ ስራ ሳይሆን ታቅዶ የሚሰራ የዘወትርና ተገምግሞ ውጤቱ የሚታወቅ ስራ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም መንግስትም የሃይማኖት መሪዎችም በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ተብሏል፡፡ ሴኩላሪዝም ብዙሃነትን ከማክበር ጋር የተያያዘ ጽንሰ ሃሳብ ስለሆነና በህገመንግስቱ ውስጥ ከበርካታ መብቶች ጋር የተጠቀሰ ስለሆነ መርሆውን ማክበር ይጠበቃል፡፡ ሴኩላሪዝም ሀይማኖት አልባ የሚያደርግ ሳይሆን የመርሁ መከበር ለሰላማችንና ለህልውናችን መሰረት መሆኑ ተገልጽዋል፡፡ የሃይማኖት መብዛት ችግር አይሆንም ወይ የተባለው ለዜጎች ያልተገደበ የማመን መብት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም የሃይማኖት የመደራጀት መብትም አላቸው፡፡ በያንዳንዱ እምነት በስተጀርባ ህዝብ ስላለለ ያልአገባብ መብቶች እንዳይጣሱ የማቻቻያ ስርዓቶችን እያሰቡ መስራት ይጣይቃል፡፡

የታባለ ሲሆን ሙስናን የሚጠየፍ ለአገሪቱ ሰላምና ብልጽግና የቆመ ትውልድ መፍጠር ከሁሉም እንደሚጠበቅም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡