Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰላም ስራዎችን ራሳቸው አስችለው እንዲሰሩ ጠየቀ

የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ኮሚኒኬተሮችን እና የአስተዳደርና ጸጥታ  ሃላፊዎችን  አወያይቷል፡፡

NEWSየፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ከዘጠኙ ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬተሮች፣ አስዳደርና ጸጥታ ሃላፊዎች ጋር ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2009 ዓ.ም አዳማ ከተማ ውይይት አድርጓል፡፡

ለውይይት  መነሻ የሚሆኑ  አራት ሰነዶች በመድረኩ የቀረቡ ሲሆን እነዚህም አንኳር ርእሰ ጉዳዮችም  የግጭት  መከላከል እና አፈታት ምንነትና ዋና ዋና ተግባራት፣ ሕገ-መንግስት እና የፌዴራል ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ፣ የሃይማኖት ተቋማትና የሚዲያ አካላት በሰላም አብሮ ስለመኖር ያላቸው ሚና እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ሚና የህገመንግስት መርሆዎችንና  ፌዴራሊዝምን ከማስረጽ አንጻር የሚሉት ናቸው፡፡

ውይይቱን የመሩ በፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የግጭት መከላከልና አፈታት ዳይሬክቶሬት ጀኔራል አቶ ሲሳይ መለሰ በሀገሪቱ ግጭቶችን በመከላከል  ላይ ያተኮሩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጹ ሲሆን ከሰላም እሴት ግንባታ አኳያ የሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመደረሱን  ተናግረዋል፡፡ለዚህም ከህብረሰተሰቡ አስተሳሰብ ለውጥ ላይ መሰራት እንዳለበትና ለዚህም የኮሚኒኬተሩ ሚድያን ተጠቅሞ ግንዛቤ እንዲዳብር ከማድረግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

"የግጭት  መከላከል እና አፈታት ምንነትና ዋና ዋና ተግባራት" የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት የሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክተር Newsአቶ ሰይድ መንዲስ እንዳሉት በግለሰብ፣  በቡድንም ሆነ በህብረተሰቡ መካከል ያለው ግንኙነት በስምምነት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አልያም ልዩነቶች በውይይት ብቻ ከተፈቱ ሰላም መሆን ይቻላል፡፡ ለዚህም የአመለካከት፣የባህሪ፣የእሴቶች ስብስብና የአኗኗር ዘይቤ የሆነው የሰላም እሴት መገንባት አስፈላጊ መሆኑንና የሰላም ባህል የሚጀምረውም ከአስተሳሰብ እንደሆነም በገለጻቸው አንስተው አስተሳሰብ ሰላም ሲሆን የእርስበርስ ግንኙነት ሰላም እንደሚሆን ነው የገለጹት፡፡

በአጎራባች ማህበረሰቦች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በመፍታት ረገድም  የተገኙ ውጤቶች እንዳሉ ጠቁመው የሰላም እሴት ግንባታ ዋና ምሰሶ ተደርጎ የሚወሰደው አለመግባባቶችን በውይይትና መሰል አማራጮች የመፍታት ባህልን  ለማጎልበት የተከናወኑት ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረሳቸው በገለጻቸው አንስተዋል ፡፡

በመሆኑም ግጭቶችን በመከላከልና በመፍታት ረገድ የአመለካከት ቁመና ላይ መድረስ አስፈላጊ   መሆኑና በዚህ ዙርያ የሚታዩ Newsክፍተቶችን መሞላትም እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ሰላም ልዩነቶችን በማቻቻል ለሁሉም ሕዝቦች ፍትህ ነፃነትና ክብር ለማጎናፀፍ ወሣኝ  መሆኑንና የሠላም እሴት መገንባት የመቻቻል እሴቶችን ይገነባል፣ ከሁከት ነፃ የሆነ ግንኙነት ስለሚፈጥር ህብረተሰቡ በመከባበርና በመፈቃቀር ያለመግባባቶችን ወይም ግጭቶችን እንዲፈታ ያስችለዋል ነው ያሉት ፡፡በተለይ የቅድመ ማስጠንቀቂና ፈጣን ምላሽ ሥርዓቱ ስኬት በህዝብ ተሳትፎ እና በየደረጃው ባለው አመራር ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የገለጹት ዳይሬክተሩ የሰላም አደረጃጀቶችንን ማጠናከር፣ የቅድመ መስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርአቱን ማስቀጠል፣ያልተፈቱ የአስተዳደራዊ ወሰን ችግሮችን ማጠናቀቅ፣ ተጎራባች ማህበረሰቦችን በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ማስተሳሰር፣ የሰላም የግጭት መከላከል ስራዎቻችንን ከሚዲያ አካላት ጋር ጥብቅ ቅንጅት መስራት የቀጣይ የትኩርት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

እና የፌዴራል ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ››የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት ፌዴራልዝም ስርጸት ዳይሬክተር አቶ ጫኔ ገበየሁ ህገ መንግስት የህግና የፖለቲካ ሰነድ ነው ያሉ ሲሆን ፖለቲካዊ ሰነድ የሚሆነው የመንግስትን ስልጣን የሚይዝ አካል የሚከተላቸውን አስተሳሰቦችና የፖሊሲ አማራጮች በማካተቱና የሕግ-ሰነድ ሆኖ የሚያገለግለው ደግሞ ዜጎች መብቶቻቸውን እንድያስከብሩና ግዴታዎቻቸውንም እንድወጡ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን ስለሚይዝ ነው፤ ብለዋል፡፡

Newsለዘመናት ሲንከባለል የኖረውን የማንነት ጥያቄን ለመመለስና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተመሰረተው ህገመንግስት አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ መገንባት ዋነኛ ዓላማው አድርጎ በሁለት የአስተዳደር አርከን የጋራና የራስ አስተዳደር ተልእኮን ለማሳካት የሚፈጠር ስርዓት፣ ፌዴራሊዝም የተጻፈ ህገመንግስት ያለው፣ የህገመንግስት  ጉዳዮች የመወሰን  መብቱ የፌዴሬሽን ም/ቤት የሆነ፣ በአባል መንግስታት መካከል ግንኙነት ያለውና ለብሄር ብሄረሰቦች ያልተገደበ መብት የሰጠ፣ የግለሰብና የቡድን መብት አጣምሮ የሚስተናግድ፣ በአነስተኛ ቁጥር የሚወከሉ ማንነቶች ጥበቃ የሚደረግበት የህብረብሄራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓትን አገሪቱ እንደምትከተል ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የስርዓቱ ስኬቶች መሰረታዊ የዜጎች ጥያቄዎችን መልሷል፣ በዚህም ማንነቶችና ባህሎቻቸውን እውቅና ሰጥቷል፣ በርካታ የልማት አውታሮች ተዘርግተዋል፣ በማኅበራዊ አገልግሎትም ዘርፈ ብዙ ስኬቶችም መመዝገባቸውና በተቃራኒው በስርዓቱ ላይ የግንዛቤ ክፍተት መኖሩ፣ የህገመንግስቱ መርሆ አተገባበር ላይ የሚታዩ ክፍተቶች፣ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችና ብልሹ አሰራር የስርዓቱ ተግዳሮቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት፣ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ፣ በፌዴራል ስርዓቱ ላይ የሚነሱ አስተሳሰቦችን አለባብሶ ከማለፍ ለይቶ ከነባራዊ ሁኔታው ጋር በማስተሳሰር መተንተን፣ የአስተሳሰብ ብዘሀነትን ማስተናገድ ለተግዳሮቶቹ በመፍትሄነት ቀርበዋል፡፡

"ሕገ-መንግስት እና የፌዴራል ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ" የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት የሃይማኖትና አምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ባለሙያ  አቶ ቢታው ታደሰ በበኩላቸው ሃይማኖት ለሰላምና ለአብሮነት ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ ካጐለበትነው ለአገራችን ልማትና ዕድገት ለማቀላጠፍ ወሳኝ እንደመሆኑ ሁሉ  በተቃራኒው  ሃይማኖትን ለኪራይ ሰብሳቢነት፣ ለአቋራጭ የፖለቲካ ስልጣንና መንግስታዊ ሀይማኖት ወይም ሀይማኖታዊ መንግስት ለመመስረት ፍላጐት ያላቸው አካላትም መጠቀሚያ ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገንዘብና መከላከልም  እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

Newsብዝሃነቶች በአንድነት የኖሩበትን የማኅበራዊ ኑሮ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነትና ስርዓት የሆነው በሰላም አብሮ መኖር ብዝሃነትን በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድን ብቻ ሳይሆን በሰዎች ህሊናና ሕልውና ላይ ሞራላዊ ግዴታም ጭምር የሚጥልና ሁሉም ሃይማኖቶች ከሚያስተምሩት ወርቃማ ሕግም ጋር የሚጣጣም መሆኑም አስረድተዋል ፡፡በሰላም አብሮ መኖር ብዝሐነትን  እንደነባራዊ  ሁኔታ መቀበል፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የትግል ስልት መከተልና  የብዝሃነቶች ነጻነትና እኩልነት  ማረጋገጥ የሚሉ ሶስት አስተሳሰቦች ጥምረት መሆኑን  በማብራሪያቸው ያስቀመጡት አቶ ቢተው  ማህበራዊ ትስስርና መደጋገፍን እንደሚያጎለብት፤ በብዝሃነቶች ውስጥ የሚፈጠሩ የልዩነት ሐሳቦች በዲሞክራሲያዊና በሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ የሚያስችል፤ብዝሃነቶች በእኩልነትና ነጻነት የሚፈልጓቸውን አስተሳሰብ እንዲያራምዱ ሰፊ ዕድል  እንደሚከፍትና ብዝሃነቶች ነባራዊ መገለጫና ፀጋ እንጅ የስጋት ምንጭ አለመሆናቸውን ሕብረተሰቡ ተገንዝቦ እንዲንከባከበው የሚያስችል መሆኑን ይናገራሉ፡፡

"የመገናኛ ብዙሃን ሚና የህገመንግስት መርሆዎችንና  ፌዴራሊዝምን ከማስረጽ አንጻር" የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አቶ አብይ የመገናኛ ብዙሃን  ሚና፣ የሃገራችን የመገናኛ ብዙሃን የሕግ ማዕቀፎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ሚና የህገ መንግስት ተልዕኮ ከመወጣት አንጻር፣ ሕገ መንግስቱንና ፌዴራሊዝምን ከማስረጽ አንጻር ሚዲያው የሚገኝበት ሁኔታ የሚሉ ነጥቦች ላይ ዳሰሳ ያደረገ ገለጻ አቅርበዋል፡፡

NEWSበቀረቡት ገለጻዎች ላይ ተሳታፊዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን የግል ፍልጎት የማንጠባረቅ ሁኔታ አለ፣ በወጣቱ ላይ ምክንያታዊ ያለመሆን ባህሪ ይታያል፣ ክልሎች በትምህርት ቤት ላይ መስራት አለባቸው፣ችግሮችን በጊዜው ባለመፍታታቸው የአገር ችግር እየሆኑ ነው፣ የግጭት ገጽታች ዶክሜንት ተደርጎ መቀመጥ አለበት፣ እድገቱ ሚዛናዊ አድረገን መስራት አለብን፣ ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት አለበት፣ የሃይማኖቶች መሰነጣጠቅ እልባት ቢሰጠው፣  የራስ አስተዳደርና ጋራ አስተዳደር ሚዛናዊ መሆን አለበት፣ የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች በዝተዋል፣ ሚድያዎች ብዝሃነትን ማስተናገድ ሲገባቸው የአንድ ወገን ልሳን ሆነው የማገልገል ሁኔታ ይታያል፣የቴሌቪዝን ሽፋን የሌላቸው ክልሎች አሉ፣ የክልል ብሮድካስቶች አገራዊ ጉዳዮችን አያካትቱም፣ የሚሉ አስተያቶች የተሰጡ ሲሆን መብራሪያም ተሰጥቷል፡፡

በዚህም የግጭት ምልክቶች ሚስጥር አይደሉም በጊዜው መረጃ ተለዋውጦ ወደ ሁከት ከመቀየራቸው በፊት መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ግጭት አይቀሬ ነው፡፡ነገር ግን የሰላም እሴት በመገንባት በውይይት የሚያምን ህብረተሰብ በመፍጠር ግጭትን መቀነስ ይቻላል፡፡ክልሎች ከቀበሌ ጀምሮ የሁነቶች ክስተትን በንቃት መከታተል ስራ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መስራት አለባቸው፣ለሰላም ስራ የበጀትና ግብአት ማሟላት አለበት፡፡እንደ አገር የተለዩት 46 የግጭት ክስተቶችን ለመድፈን እንደሚሰራም ተገልጸል፡፡

በመጨረሻም የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን፣ የፌዴራሊዝምን የበሰላም አብሮ መኖር ዙርያ ራሱ አስችሎ የሚሰራ የፕሮግራም ለማሰራት ከሃላፊዎች ጋር ከስምምነት መድረስ፣ በክልል ደረጃ  የመንግስት ኮሚኒኬሽን፣ የአስተዳደርና ጸጥታ እንዲሁም  የብዙሃን መገናኛ  በቅንጅት እንዲሰሩ፣ በፌደራል ደረጃ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤትና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባስልጣን የጋራ ፎረም በመመስረት የጋራ እቅድ በማቀድ በጋራ መስራት አንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን የሚድያ አካላትን አቅም የማጎልበት ስራ ትኩረት ተሰጥቶት አንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቶ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡