Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲ የሰላም ፎረሞችን በዩኒቨርሲቲዎቹ የሰላም ስራዎች ዙርያ አወያየ

Newsከየካቲት 3 እስከ 5 ቀን 2009 ዓ/ም በአዳማ ከተማ የተካሄደው የዘጠኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ፎረም አባለት የምክክር መድረክ የከፈቱት የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን ፈይሶ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ለአገራችን የማይነጣጠሉ የህልውና ጉዳዮች ናቸው፡፡ካሉ በኋላ ሰላም ግን እጅግ አሰፈላጊና ለሁሉም መሰረት ነው ያሉት፡፡ይህም የሚታወቀው የሰላም እጦት ሲገጥም እንደሆነ ገልጸው ለመኖርም ሆነ ለመማር ቅድሚያ ሰላም መጠበቅ እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች በተነሳው ግጭት የሰላምን እጦት ማየት እንደተቻለ የሚያስታውሱት አቶ ሁሴን በተለይ በርካታ ወጣቶችን ይዘው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ግንባታ ስራ መጠናከር እንዳለበት ነው መልእክት ያስተላለፉት፡፡

በየዩኒቨርሲቲው ከሚታዩ ችግሮች ትምህርት በመወስድና ያሉዋቸውን ጠንካራ ጎኖችን ይዘን ለመቀጠል ጠቃሚ መድረክ መሆኑንም በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡

የግጭት መከላከል አፈታት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሲሳይ መለሰ ባቀረቡት ሰነድ ላይ እንደገለጹት ሰላምና ግጭትን መረዳት እንዲሁም የሰላም እሴትን ማዳበር ለሰላም ግንባታ ያለውን ፋይዳ ከፍተኛ መሆን ነው፡፡ሰነዱ ላይ የሰላም እሴት አጠቃላይ ምልከታ በኢትዮጵያ በሚለው ርእስ ስር እንደተገለጸው የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ዋነኛው የሰላም እሴት ግንባታ ምሰሶ መሆኑ፣ በግጭት ተጋላጭ አካባቢዎች የተዋቀሩ የሰላም አደረጃጀቶች፣ አገሪቱ የምትከተለው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ መስመር እና ከሱ የመነጩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ልማትም ይሁን ሰላምን በመገንባት ረገድ የራሳቸው ድርሻ እንደሚወጡ ነው የተገለጸው፡፡

በአገሪቱ ለሰላም ባህል አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ነባራዊ ሁኔታዎችና አቅሞች እንዳሉ ሁሉ የተዛባ አመለካከትና ቅድመ ትንበያ፣ ጅምላ ፍረጃና አድልዎ የሰላም ባህሉን የሚጎዱ አሉታዊ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች እንዳሉ የገለጹት ዳይሬክተሩ እነዚህን ዝንባሌዎች ማስወገድ እንደሚገባ፣ ሴቶች ወጣቶችና የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ሀይል ስለሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራባቸው አስምረውበታል፡፡በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የዩኒቨርሲቲ ወጣቶች የሰላም አምባሳደር ሆነው መውጣት እንዳለባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የግጭት ዓይነቶችና የሂደት ደረጃቸው ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ግጭት ሲከሰት ዉይይት፣ ድርድር ሽምግልና እና ዕርቅ የግጭት መፍቻ አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ሰላምን ማምጣት እንደሚጠበቅ ነው አቶ ሲሳይ ያስገነዘቡት፡፡

የሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ሰይድ መንዲስ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰላም ፎረም ማቋቋሚያ መመሪያን በመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ የግጭት መከላከልና አፈታት ሥራን ውጤታማ በሆነ መልኩ በማካሄድ ግጭቶች ሊያስከትሏቸው የሚችሉትን ጉዳቶች መቀነስ እንዲሁም ግጭቶች ተከስተው ጥፋት ከማድረሣቸው በፊት የመከላከል ሥራ በማከናወን የሰላም እሴት ግንባታን በሕብረተሰቡ የማስፋት ሥራን እንደዋነኛ ግብ ይዞ የተቋቋመ መ/ቤት መሆኑ ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ግብ ስኬታማነት የሚረዱ የሠላም ፎረሞችን በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ማደራጀት የሠላም እሴት ግንባታ ሥራዎችን በማከናወን፣ ያለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት፣ ተማሪዎች በመቻቻልና በመከባበር ለጋራ ጥቅም እንዲቆሙ የሚያሥችል ግንዛቤ የማስጨበጥ አስፈላጊነት እንደላቸው ነው ያስረዱት ፡፡የሰላም ፎረሞች በየዩኒቨርሲዎቹ ዋና ግቢና ቅርንጫፍ ካላቸውም ቅርንጫፍ ግቢዎቹ የራሳቸውን ፎረም እንደሚያቋቋሙ የገለጹት ዳይሬክተሩ የሰላም ፎረሞች ህብረት ላይ መሳተፍ እና ከሌሎች ዩኒቨርሲቲ የሰላም ፎረሞች ጋር የልምድ ልውውጥ እንደሚካሄድም ገልጸዋል፡፡የሰላም ፎረሞቹ ተጠሪነታቸው ለየዩኒቨርስቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች ሲሆን ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሰላም ፎረም ሰብሳቢ እና ም/ሰብሳቢዎችን ያቀፈ የሰላም ፎረሞች ሕብረት እንደሚቋቋም ታውቋል፡፡

NEWSከዚህ በተጨማሪም የፎረሞቹ አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት፣ የፎረሙ ሥራ አስፈፃሚ አባላትና ስብጥር፣ የፎረሙ አባላት መብትና ግዴታ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ መምረጫ መስፈርት፣ የግንኙነት ጊዜና ርእሰ ጉዳዮች አስመልከቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡የሰላም ፎረም ህብረት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የኒቨርሲቲ ቦርዶች፣ ዩኒቨርስቲዎቹ የሚገኙበት ዞኖች እንዲሁም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተግባርና ሃላፊነትን ያስተዋወቁት ዳይሬክተሩ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን ተግባር በቅንጅት እንዲፈጽሙና ሃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በቀረቡት ገለጻዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል በርካታ ሀሳቦችም የተንሸራሸሩ ሲሆን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰላም ፎረም ማቋቋሚያ መመሪያው ግብአት የሚሆኑ ነጥቦች ማግኘት ተችሏል ፡፡

የሰላም ፎረም እንኳ መኖሩ የማያውቁ የዩኒቨርሲቲ ብርዶች አሉ፣ ሴቶችን እናሳትፍ ሲባል የማሳተፍ መጠኑ በፐርሰንት መቀመጥ አለበት፣ በአመለካከት ላይ ባለመሰራቱ መምህራን በፎረሙ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት አይታይባቸውም፣ ፎረሞቹ እንደ የፖለቲካ ስራ የማየት ሁኔታ አለ፣ የዩኒቨርሲቲውን ህግ በመተላለፍ ግጭት የሚፈጥሩ አካለት ላይ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ባልተሰራበት ሰላምን ማስጠበቅ ይከብዳል እና ሌሎች አስተያየቶችን  ተሳታፊዎች የነሱ ሲሆን ማብራሪያም ተሰጥቷል፡፡ይሄውም ዬኒቨርሲቲ የሰላም ፎረሞች ግጭቶች ከመፈጠራቸው ቀድሞ የመከላከል ስራ ነው የሚሰሩት፡፡ስራቸው የሰላም ግንባታ ስራ ነው የተባለ ሲሆን ልዩነቶችን ለማጥፋት ሳይሆን ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ በፈትቶ ወደሚያስማመ ነጥብ በመድረስ ሰላም ለማምጣት መሆኑም ተገልጸል፡፡