Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

የአርብቶ አደሩ የሠላምና የልማት የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለህዳሴያችን

የ16ኛው የአርብቶአደር በዓል ተከብሯል

NEWSበኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ለሶስት ቀናት እየተከበረ የቆየው 16ኛው የአርብቶአደር በዓል ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም በጂግጂጋ ስቴዲየም በተደረጉ ልዩ ልዩ ስነስርዓቶች ተጠናቋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ሃላፊዎች፣ ሚኒስተሮች፣ የኢጋድ ተወካዮች፣ የአራቱ አርብቶአደር ክልል ርእሰ መስተዳድሮች፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአርብቶአደር ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ሴክተር መ/ቤት ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ ሙሁራን፣ ተማራማሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአርብቶ አደሩ ተወካዮችና ሚዲያዎች  በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡

NEWSየሱማሌ ክልል ርእሰ  መስተዳደር አቶ አብዲ መሀመድ  በክልሉ የተሰሩ የልማት ሰራዎች ማለትም በመንደር ማሳባሰብ፣ በግብርናና በጤና ኤክስቴንሽን፣ የመጠጥ ውሃ፣ የትምህርት ተደራሽነትና በመሰረተ ልማት  ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን  ገልጸው ስራዎቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት፡፡አያይዘውም በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሰውና በእንስሳት የደረሰው ጉዳት በፌዴራል ድጋፍና በክልሉ በተሰሩ የመከላከል ስራዎች በተለይ የሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በራስ አቅም መቋቋም መቻሉን ነው የገለጹት፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሃይለማርም ደሳለኝ ድርቅ በመታው አካባቢ  ተገኝተው ላደረጉት ጉብኝት አቶ አብዲ ያመሰገኑ ሲሆን ከፌዴራልና ከትግራይ ክልል ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

Newsየፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር አቶ ካሳ ተክለብርሃን የአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ድርቅና ግጭት የሚፈጠርባቸውና በከፋ ኃላቀርነት ላይ መቆየታቸውን አስታውሰው ባለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት አስተማማኝ ሰላምና መልካም አስዳደርለማረጋጋጥ እንዲሁም  አገሪቱ እድገት ጋር ተመጣጣኝ ደረጃ ለማድረስ በአካባቢዎቹ መንደር ማሰብሰብ ፕሮግራምን ጨምሮ ዘረፈ ብዙ ስራዎች በመሰራታቸው ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡ይሁን እንጂ የህዝቡ ተጠቃሚነት ባለመረጋገጡ የድርቅ ተጋላጭ እየሆነ እንደሚገኝ የገለጹት ሚኒስትሩ የድርቁን አደጋ ለመታደግ ቢቻልም ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከል የጋራ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ  አስተላልፈዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት የልማት ድርጅት ተወካይ አቶ  ኤሊሳዲግ አብደላ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሉት በስምንት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተመሰረተው ኢጋድ  የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በእርሻ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ልማት ትብብር የማጠናከር ዓላማ ያለው ሲሆን  የኢትዮጵያ አርብቶአደር በኣል የቀጠናውን አርብቶ አደር ማህበረሰብ የሚያስተዋውቅ በመሆኑ ኢጋድ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት በጣም ፍቃደኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ኢጋድ ስትራቴጂ ፕሮግራም ነድፎ ድርቅ አደጋ መቋቋምና ዘላቂ  ስራዎች እቅድ  (IDDSRSI) በቀጠናው በጋራ ለመስራት መታሰቡንና ለዚህም የኢትዮጵያ አርብቶአደር ፎረም በአጋርነት እንደሚሰራ  ተናግረዋል፡፡የአርብቶአደሮች በኣል ለበርካታ ዓመታት መከበሩን ያደነቁ ሲሆን መላ አርብቶአደሮች ተገናኝተው ለመወያየት፣ ልምድ ልውውጥ ለማድረግና የጋራ አቋም ለመያዝ ትልቅ ፋይዳ ያለው መድረክ መሆኑንም  ገልጸዋል፡፡

NEWSየኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሃይለማርም ደሳለኝ በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶችና መሰረተ ልማት ግንባታ ከእቅድ እስከ ትግበራ አርብቶ አደሩን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥቶ በመሰራቱ ህዝቡን ከመንግስት ጎን ማሳለፍ መቻሉን  በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡በተለይ መንደር ማሰባሰብ ፕሮግራሙ በአርብቶ አደሩ ሙሉ ፍቃደኝነትና የተሟላ ዝግጅት የተጀመረ በመሆኑ የውሃ አቅርቦት፣ የእርሻ፣ የግጦሽ መሬትና ማህበራዊ ተቋማትን በማሟላት ወደ  ዘመናዊ አርብቶአደርነት ለማሸጋገር ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥራትና ፍጥነት ጋር ተያይዞ በሂደቱ የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ያነሱ ሲሆን መጓተቶች፣ የአቅርቦት እጥረትና ሙስናን መታገል እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡ የተቀመጠውን የአርብቶ አደር የልማት አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ተቋም በመገንባት፣ በቅንጅት በመስራት፣ በአካባቢዎቹ ዘላቂ አቅም ከመፍጠር አኳያ የአርብቶ አደር  ወጣቶችና ሴቶችን ትኩረት አድርጎ ከተሰራ ልማቱ ተመጣጣኝ እየሆነ ስለሚመጣ አስተማመኝ ሰላምም ይረጋገጣል ነው ያሉት፡፡

በእለቱ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጥቅሉ 394 ከየክልሉ ተመርጠው የመጡ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ታታሪ የልማት ጀግና አርብቶአደሮችና ድርጅቶች እውቅና የሰጡ ሲሆን ከበዓሉ ቀድም ብሎ በተደረገው የጉብኝት ፕሮግራም በፋፈን ዞን የቀብሪበያህ ወረዳ ቆሃ ቀበሌ የሰውና የአንስሳት መጠጥ ውሃ ተጎብኝቷል፡፡ባለፈው ዓመት ጀምሮ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ከተሰሩ ስራዎች መካከል የእንስሳት መኖ በማልማት የተገኘውን የመኖ ምርት ማየት ተችሏል ፡፡

Newsየአምደሌ ኳረንቲን ሌላኛው የጉብኝት መዳረሻ  የሆነ የልማት ስራ ሲሆን በ75 ሚሊዬን ብር የተገነባውና የዳልጋ እንስሳትን ማቆያ የሆነው ኳረንቲኑ ስራ ሲጀምራ ከ32 ሺህ እንስሳትን በመያዝ ለግብይት ማቅረብ የሚስችል መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ከተደረገው ገለጻ  መረዳት ተችሏል፡፡

ከዚህ ባሻገር የጂግጂጋ የስጋ ማቀነባበሪ የተጎበኘ ሲሆን የፎቶግራፍና አውደርእይና ባዛር ተከፍቶ ለእይታ በቅቷል፡፡ በተጨማሪ የ16ኛው አርብቶ አደር በዓል ምክንያት በማድረግ የተካሄደው የምርጥ ተሞክሮ ልውውጥ ፕሮግራም ላይ የአፋር ዘመናዊ የመኖ ልማት፣የደቡብ መንደር ማሰባሰብ በአርብቶ አደሩ አካባቢ፣የቦረና ምርጥ ዘር ማዳቀልና ባህላዊ የመኖ ልማት በኦሮሚያ ክልል ፣ የሱማሌ የውሃ ፕሮጀክት ልማት ላይ ምርጥ ተሞክሮዎች ሆነው  ቀርበዋል፡፡የአርብቶ አደሩን ችግር የሚፈታ የአውደ ጥናትም በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ቀርቧል ፡፡

የበአሉ በማጠቃለያ እለት ላይ ሰቴድየም ላይ የተደረገው ስነስርዓት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአርብቶ አደሩ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡

ቀጣዩን የ17ኛው የአርብቶ አደሮች በዓል አዘጋጅ ለሆነው የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል የአርማ ርክክብ የተደረገ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ 15ኛው አርብቶ አደር በኣል መከበሩ  የሚታወስ ነው፡፡