Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለመፍታት ሴቶችን ማብቃት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

Newsልዮ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች የሚገኙ ሴት የመንግስት ሰራተኞችን አቅማቸውን በማሳደግ ብቁ ተወዳዳሪና ውሳኔ ሰጭ ለማድረግ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በልዩ ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ፕሮግራሙን በንግግር  የከፈቱት የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን  ሲሆኑ  ሴቶች ለረዥም ዘመናት ይደርስባቸው በነበረው አድልኦ ምክንያት ከፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዩች ተገለው ኑረዋል፡፡በአሁን ወቅትም ችግሩ ስር የሰደደ በመሆኑ ሴቶች በሁሉም መስክ የሚፈለገውን ያህል ተሳታፊ እንዳልሆኑ ገልጸዋል፡፡ በተለይ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና አሁንም ድረስ ያልተቀረፈ ችግር ነው፡፡ይህንንም ችግር ለመፍታት ሴቶችን በየደረጃው በማስተማር ከአመለካከት ጀምሮ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን  ክፍተት በመሙላት ሴቶችን ወደ ውሣኔ ሰጪነት ማምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡  

ልዮ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ጹሁፍ በፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ ተገኝ የቀረቡ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ባለፉት ስርዓቶች ሲከተሏቸው የነበሩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በአገራችን አንድ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማኀበረሰብ የመፍጠር ራዕይም ይሁን ተልእኮ ያልነበራቸው ከመሆኑም በላይ ለሠላም፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ሥራዎች እንቅፋት የሆኑ አመለካከቶችን እና ተግባሮችን አስፋፍተው አልፈዋል፡፡ይህም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መካከልም በከፋ ደረጃ የሚገለጽ ያልተመጣጠነ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ስለሆነም ልዮ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች በተነጻጻሪ ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ ሁኔታ በልማትና በእድገት እጅግ ወደ ኋላ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል  ብለዋል፡፡በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሳቢያ በሴቶች ላይ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች በርካታ ሲሆኑ ዋነኞቹ የብልት ትልተላ ፣ከፍተኛ ጥሎሽ ለማግኘት ሲባል ያለዕድሜ ጋብቻ በወር አበባና  በወሊድ ጊዜ ሴቶች ከቤት ውጭ እንዲቆዩ መደረጋቸው፣ የለውጥ፣ የውርስ ጋብቻ፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ በስፋት ይታያል፡፡እንዲሁም በአገራችን ሴቶች ከፍተኛ የስራ ጫና ያለባቸው  ቢሆኑም ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ጎልቶ የሚታይ ሲሆን  በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ባሉ ስራዎች ዋነኛ ተዋናኝ በመሆናቸው በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሚፈለገውን ያህል ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ 

ወ/ሮ አበባ እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ መንግስት ልዩ ፕሮግራም ቀርጾ ህብረተሰቡን በመንደር በማሰባሰብ በመሰረተ ልማት ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ተመጣጣኝ ልማት የማረጋገጥ ስራው  ዋነኛ መነሻው በተጨባጭ የሚታየው የልማትና የአቅም ክፍተት እና በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው ልዩ ድጋፍ የሚሹ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የልማት ተጠቃሚ የማድረግ ህገ-መንግስታዊ ግዴታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ስለሆነም ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት በማምጣትና በሂደት በወሳኝ የልማት፣ Newsየማኀበራዊ አገልግሎትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ከተሻሉ አጐራባች ክልሎችና  ከአገራዊ አማካኝ (National Average) ጋር በማመጣጠን በክልሎቹ መካከል  የሚታየውን የልማትና የአቅም ክፍተት ለማጥበብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ተመጣጣኝ ልማት የማረጋገጥ ስራዎች እንደየ ክልሎቹ ነባራዊ ሁኔታ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት የማረጋገጥ መርህን ተከትሎ ቁልፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር ክፍተትን በጋራ በመለየት ክፍተቶችን ለመሙላት በወሳኝና መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጡ የግብርና፣ የውሃ፣ የጤና፣ የትምህርትና የሲቪል ሰርቪስ (High Impact & Citical Targates) ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላመጡ ሶስት ተማሪዎች ሽልማትና እውቅና የተሰጠ ሲሆን የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር አቶ ካሳ ተክለ ብርሀን ያገኘነውን እውቀት በየምንሰማራበት አካባቢዎች በማስፋት ሴቶች ላይ ያሉ የተለያዩ ጫናዎችን በማቅለል የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለመቅረፍ ሴቶች መሪ ተዋናይ በመሆናቸው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሴቶችን በማካተት ማብቃት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡