Press and Media Press and Media

News Archive News Archive

Back

የ16ኛው የአርብቶአደር በዓል ሊከበር ነው

"የአርብቶ አደሩ የሠላምና የልማት የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለህዳሴያችን!"

በሚል መሪ ቃል የ16ኛው የአርብቶአደር በዓል ከጥር 15 እስከ 17 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሱማሌ ብሄራዊ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት ይከበራል፡፡

በበዓሉ እለት በእስቴድየም ከሚደረገው ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ንግግርና የሞዴል አርብቶአደሮች ሽልማት ስነስርዓት ባሻገር  የልማት ቦታዎች ጎብኝት፣ የምርጥ ተሞክሮዎች ልምድ ልውውጥ፣  የፎቶግራፍ ኤግዚብሽን፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአርብቶአደሩ ተወካዮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት እና ሌሎች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ፡፡

ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና ተወካዮች፣ የፌዴራልና የአራቱ አርብቶአደር ክልል ርእሰ መስተዳድሮች፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአርብቶአደር ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ ሙሁራን፣ ተማራማሪዎች እንዲሁም ዲፕሎማቶችና የሚዲያ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመድረኩ የሚታደሙ ሲሆን ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ታላቅ ሁነት ይሆናል፡፡