የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ

የአገልግሎት ገለጻ
 • አዲስ የሚመዘገቡ፣ህብረት የሚመሰረቱ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተመሰረቱ የሃይማኖት ተቋማትን መዝገብ የምስክር ወረቀት የሚሰጥበት አገልግሎት ነው፡፡
 መሟላት የሚገባቸው ሰነዶች
 1. የአገልግሎት ጥያቄ ማመልከቻ
 2. የሀይማኖት ተቋሙ ዓይነትና ስም
 3. መመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ
 4. የመስራቾች ለመመዠገብ የወሰነበት ቃለጉባዔ
 5. የመስራቾች አጭር መረጃ በቅጽ የሚሞላ
 6. የመስራቾች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
 7. የሃይማኖት ተቋሙ ዋና አድራሻና ሊሰራባቸው ያለባቸው ክልሎች
 8. ጉዳዩን እንዲከታተሉና እንዲያስፈፅሙ በመስራቾች የተወከሉ ተወካይ
 9. የመስራቾች ብዛት(ለቤተክርስቲያን 50 ሰው ለሚኒስትሪ /ማህበር 15 ሰው (የሌላ ሀይማኖት ተቋም አናል ያልሆኑ)
  የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች
 • ከላይ በተራ ቁጥር ሦስት የተመለከቱት ሁኔታዎች መሟላታቸውና ህጋዊ መሆናቸው ይመረመራል
 • የተጓደሉና የሚሟሉ ካሉ እንዲታረሙና እንዲሟሉ ይደረጋል
 • ሁሉም ሁኔታዎች መሟላታቸው ሲረጋገጥ የሃይማኖት ተቋሙ ስም (አርማ ካለ) በጋዜጣ እንዲወጣ ይደረጋል
 • ተቃዋሚ ከለሌ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ደብዳቤ ይዘጋጃል
 • የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል
 • የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ደብዳቤው ከመዝገብ ቤት ወጪ ሆኖ ለህጋዊ ተወካዩ ይሰጣል
 • በፎቶ ኮፒ ለሚቀርቡ ማስረጃዎች ዋናው ሰነድ ቀርቦ መመሳከር ይገባዋል